አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝን ጨምሮ አሉ የሚባሉ ቦታዎች በወያኔ ባለስልጣናት (ባለ ሃብቶች) በኢንቬስትመንት ስም እየተያዙ ሲሆን የአፋር ህዝብ ደግሞ እየተፈናቀለ ይገኛል፤ የአፋር ህዝብ በሰላም መኖር አልቻለም። ባለፉት 5 ዓመታት ወደ 1700 የሚደርሱ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በመንግስት የሞቱት ቁጥር ደግሞ 121 ደርሷል! አርሶ አደሩን በግዴታ በማፈናቀል መሬታችን ለውጭ አገር ባለሃብቶችና ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እየተሰጠ ይገኛል! የክልሉ መንግስት ነን የሚሉ የወያኔ ታማኝ አገልጋዮች ደግሞ የአፋር ህዝብን ሰብዓዊ መብትን ማስጠበቅ አልቻሉም።
ይህ በእንዲህ እያለ በሰሜናዊው የአፋር ክልል በዳሉል ወረዳ 13 አመት ያለ መንግስት የሚኖሩ አፋሮች እንዳሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀው የሚገባ እውነት ነው!
ቦታው ሰውነ ወይም “ጊሊስ” ይባላል፤ የዳሉል ወረዳና የትግራይ ክልል ድንበር ስትሆን በደርግ ጊዜ የዳሉል ወረዳ ም/ቤት የነበረበት ቦታ ነው! ቋንቋቸው፤ በህሊናቸው እና ሃይማኖታቸው አፋሮች እያሉ ሰብዓዊ መብታቸው አለገኙም ወያኔ ስልጣን በያዘበት ጊዜ እኛ አፋሮች ነን መብታችን ይከበረልን ቢሉም ሰሚ አላገኙም የአፋር ክልል መንግስትም ቢሆን እናንተ ትግሬዎች ናቹ አናውቃቹሁም ብለዋቸዋል።
ይህ ህዝብ ለ13 አመት ዲሞክራሲም ሆነ ሰብዓዊ መብት ያላገኙ ግን የሕወሓት ጭኮና ያልተቀበሉ መንግስት አልባ ህዝብ ሆነው ይገኛሉ! በኢትዮጲያ ህገ-መንግስት አንቀፅ 46 እና 48 ይከበረልን! በህግ መንግስት ላይ ማንኛውም ህዝብ በቋንቋቸው የመማር የመናገርና የመፃፍ መብት እንዲሁም ባህላቸው የማሳደግ መብት አላቸው ይላል።
በተግባር ግን እውነታው ይሄ ነው !!!
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34263
No comments:
Post a Comment