Opposition Voice

Opposition Voice

Saturday, May 24, 2014

የኢህአዴግ የ23 ዓመት “ፌዴራላዊ የዘር አወቃቀር” ውጤት



ዘረኝነት - በኢትዮጵያ እግር ኳስ!
tok
የጋምቤላ ምርጥ “ቶክ” አንገቱን ደፋ
የኢትዮጵያው ቡናው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የጋምቤላ ምርጥ ውጤት ቶክ ጀምስ ይርጋለም ላይ በአንዳንድ የሲዳማ ደጋፊዎች በዝንጀሮ ድምፅ በቆዳ ከለር ተሰድቧል።
በቦታው የነበሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊው ቶክ በድንጋጤ ከሜዳው ወጥቶ የተቀያሪ ወንበር ላይ አንገቱን አቀርቅሮም ታይቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የግለሰቦች ስም እየጠሩ የሚሳደቡ እንዳሉ ይታወቃል።
በውጭ አገር ተጨዋቾች በሌሎች አገር ደጋፊዎች ከቆዳ ከለር ጋር በተያያዘ ሲሰደቡ በእኛ አገር ደግሞ ዘረኝነት በራሱ ዜጋ ሲሰደብ ከማየት ምን የሚያስደነግጥ አለ?
ቶክ በወገኑ እንደ ዝንጀሮ ተሰድቦ አንገቱ ደፍቷል፤ ይህ ነገር ወደፊት በድጋሚ እንደማይከሰት ምን ማረጋገጫ ይኖራል? (ኢቲዮኪክአፍ እናመሰግናለን)
**********
ምንጭ: ድሬ ቲዩብ ላይ ተለጥፎ በነበረ ጊዜ የተወሰደ
http://www.goolgule.com/the-result-of-eprdf-ethnic-policy/

No comments:

Post a Comment