Opposition Voice

Opposition Voice

Saturday, September 19, 2015

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል “ሕዝብ አስፈቅደን ውጊያ እንጀምራለን” ሃይለማርያም


omhajer
በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።
የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።
አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።
ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
four front mapከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።
በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
http://www.goolgule.com/tplf-starts-war-wounded-soilders-seen/

ልዩነትን በማቻቻል እና በመከባበር በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው።


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በጋራ ላለመስራት ማንገራገር እና አለመፈለግ እና በስሜት መነዳት የፖለቲካ ውጤቱ እና ጠቀሜታው ለጋራ ጠላታችን ለወያኔ ነው::የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራዊ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::
ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራዊ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር በመከባበር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
http://www.mereja.com/amharic/467436

Mola Asgedom Mission Accomplished EBC


Breaking News : Mola Asgedom Mission Accomplished - YouTube: ""

http://woyane-ethiopianism.blogspot.ch/2015/09/breaking-news-mola-asgedom-mission.html

Professor Birhanu Nega on Mola Asgedom (Must Listen)

Professor Birhanu Nega on Mola Asgedom (Must Listen)

Filed under: News,News Feature | 


ESAT Special Dr Birhanu Nega on Andargachew Tsege July 29 2014
- See more at: http://www.zehabesha.com/professor-birhanu-nega-on-mola-asgedom-must-listen/#sthash.0k2yyp4V.dpufhttp://www.zehabesha.com/professor-birhanu-nega-on-mola-asgedom-must-listen/

Eritrean activists renew calls for release of jailed officials


Filed under: News | 
By Tesfa-Alem Tekle
September 18, 2015 (ADDIS ABABA) – Some 12 exiled Eritrean campaigner groups on Friday called for the release of 11 former Eritrean officials who remain held incommunicado since a government crackdown in 2001.
JPEG - 23.8 kb
Eritrea, which borders Sudan and Ethiopia, has been dubbed the North Korea of Africa (HRW)
“We – as Eritrean organizations – demand the immediate release of the eleven signatories of the Open Letter now in detention and the implementation of the democratic reforms for which they fought” said a letter signed by the organizations and sent to Sudan Tribune.
The 11 Eritrean prominent politicians, including three former cabinet ministers who were seen as loyalists of the president were arrested on 18 and 19 September 2001 along with other suspected dissidents and journalists.
The detainees who were then serving as senior military or political leaders during the decade’s long war of independence were detained shortly after they called up on President Isaias Afewerki for democratic reform.
In May 2001 they wrote an open letter to the president and to the ruling People’s Front for Democracy and Justice (PFDJ) party, calling to implement Eritrea’s constitution , for the democratisation of government institutions, freeing of political prisoners, strengthening civil society, building new homes and aid for disabled national liberation fighters.
However the regime in Asmara responded by arresting them by accusing them of committing crimes against the security of the nation and conspiring with Ethiopia to topple President Isaias.
They have since been held incommunicado without charge for 14 years now.
In an email exchange, Feruz Werede a member of the Stop Slavery in Eritrea Campaign toldSudan Tribune that the petition letter that calls for the release of the 11 has now been circulated to the European Union.
Feruz who also is the official spokesperson of the 12 campaigner group made a call to the international community to listen to the plight of those people and their families.
“We do not know the condition of the officials arrested or their whereabouts. They have been incommunicado since their arrest 14 years ago,” she said.
International right groups say the detainees had been denied access to their families’ access to lawyers as well to medical treatment they need.
Political prisoners in the Red Sea nation are held in the country’s notorious prison facilities where inmates are subjected to extreme temperature conditions.
Former prisoners who arrived in Ethiopia recently told Sudan Tribune that most political inmates are incarcerated in underground cells and in shipping containers where temperatures could soar up to 50 Celsius.
Currently there are an estimated 5,000 to 10,000 political prisoners in Eritrea.
(ST)
- See more at: http://www.zehabesha.com/eritrean-activists-renew-calls-for-release-of-jailed-officials/#sthash.zgxO3J2z.dpuf
http://www.zehabesha.com/eritrean-activists-renew-calls-for-release-of-jailed-officials/

Monday, September 7, 2015

http://original.livestream.com/ethiopianism/video?clipId=pla_15bae76a-4325-4e1e-8b60-fbdc4fbcd5e2&utm_source=lslibrary&utm_medium=ui-thumb