Opposition Voice

Opposition Voice

Friday, January 8, 2016

የሰሞኑ “የኦሮምያ ግርግር” ግራ ገብቶኛል



የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም
oromoprotest
በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤–
አንድ፡– ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?
ሁለት፡– የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ?
አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤
ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤
አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤
ሁለተኛው ውጤት የልዩነቱ ባለቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፤ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡
አደጋው ወደሁለተኛው ጥያቄ ይመራናል፤ ገብቶኝ እንደሆነ የግርግሩ ምክንያት ሁለት ናቸው፤ አንዱ ከቤት-ንብረት መፈናቀል ነው፤ የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ነው፤ ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች ሚደፈጥጡ ናቸው፤ ልብ በሉ የኦሮሞን የዜግነት መብቶች ይደፈጥጣል አላልኩም፤ የኢትዮጵያውያንን ሁሉ መሠረታዊ መብቶች የሚደፈጥጥ ነው፤ ይህ የማያጠራጥር እውነት ነው፤ ይህንን ከተቀበልን ጉዳዩ የኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ ግርግሩም የኦሮሞ ብቻ አይደለም፡፡
ትልቁ አደጋ ያሁንን ግርግር የኦሮምያ ብቻ ካደረግነው ወደፊት ያው ጉዳይ በሌሎች ጎሣዎች መሀከል ሊነሣ ነው፤ ሌሎች ግርግሮች ሊያስፈልጉ ነው፡፡
ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው፡፡
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ታኅሣሥ 2008
http://www.goolgule.com/confused-about-the-current-oromo-protest/

No comments:

Post a Comment