“ምላሽ ካልተሰጠን የትምህርት ማቆምና ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን!”
የትምህርት ሚኒስትር በ2006 ዓ.ም በአገሪቱ በተፈጠረው የመምህራን እጥረት ምክንያት በተለ ያዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ኢትዮጵያውያንን ለአንድ አመት ሙሉ ወጫቸውን ችሎ የማስተማር ስነ ዘዴ (ፔዳጎጅ) በማስተማር ወደ መምህርነት እንዲገቡ ማስታ ወቂያ ያወጣል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረ ትም ለማጣሪያነት የቀረበውን ፈተና በመፈተን መልምሎ ለስልጠና እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት በ10 ዩኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ) እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡
ይህ ስልጠና እየተካሄደ ባለበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ሙሉ ወጫቸ ውን መንግስት እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር የመጡት፡፡ በዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ የተደለ ደሉት 330 ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ተማሪዎቹ ቃል በተገባላቸው መሰረት መቀጠል አለመቻላቸውን ነው በቅሬታ የሚናገሩት፡፡ ወደ ዝግጅት ክፍላችን በአካል መጥተው ስለሁኔታው ያስረዱት ተማሪዎች ሁኔታውን እንደሚከተለው ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ማስታወቂያውን አይተን ስራችን ለቀን ነው የመጣነው፡፡ ሆኖም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስትር ቃል በገባው መሰረት ከህዳር 23 ጀምሮ የምግብም ሆነ የቤት አገልግሎት ሊሰጠን አልቻለም፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመኝታ አገልግሎት የለም በመባሉ ደብረዘይት በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ቅርንጫፍ የእንሰሳት ህክምና እና የግብርና ኮሌጅ ለሁለት ሳምንት እንድንቆይ ተደረገ፡፡ ሆኖም ደብረ ዘይት በሚገኘው ኮሌጅ ጥቁር ሰሌዳን ጨምሮ ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ አቅርቦቶች ልናገኝ አልቻልንም፡፡››
ከዚህም ባሻገር በዚህ ወቅት ተማሪዎቹ የመብት ጥያቄ እንዲያነሱ ያደረጋቸው ሌላ ምክንያትም ተፈጠረ፡፡ ‹‹ትምህርቱ በተባለው መልኩ ሊሰጠን አልቻለም፡፡ አንድ መምህር ወደ ደብረዘይት ሄዶ የሳምንቱን የትምህርት ፕሮግራም ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት እንዲሁም ከ7 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል አስተምሮ ይሄዳል፡፡ ይህን ተከትሎም አንዳንድ የመብት ጥያቄዎችን ማንሳት ጀመርን፡፡›› ይላል አስተባባሪውና የጅኦግራፊ ተማሪው ጋሻነህ ላቀ፡፡
ተማሪዎቹ ሌላ ስራ ስለሌላቸውና ከቤተሰብ ውጭ ስለሚኖሩ አንዳንድ መሰረታዊ አቅርቦቶች እንዲሰጧቸው ለትምህርት ሚኒስትር ያሳውቃሉ፡ ፡ አያይዘውም የትምህርት እድል እንዲያገኙና በደሞዝ ጉዳይም ድምጽ አሰባስበው ያስገባሉ፡፡ ትምህርት ሚኒስትርም ‹‹እናንተ የወጭ መጋራት ስላልሞላችሁ የጠየቃችሁት አቅርቦት አይሰጣችሁም፡፡›› ይላቸዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ለሁለት ወር ከሁለት ሳምንት በላይ (ከህዳር 24- የካቲት 8) በደብረዘይት እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ ከደብረ ዘይት ሲመለሱ ይዘጋጃል ተብሎ የነበረው አልጋም ሆነ ሌላ አቅርቦት አልተዘጋጀም፡፡ ይልቁንም ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚገኝ ባዶ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ አራት አራት ፍራሽ እያነጠፉ እንዲተኙ ይደረጋሉ፡፡ ትምህርቱን ጥለው እንዳይሄዱ እስካሁን ያሳለፉትን ችግር ትተው መሄድ አልፈለጉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ትምህርት ሚኒ ስትርንና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ችግሩን እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው ንም እስከ ፓርላማና ሌሎች ተቋማት ድረስ አድ ርሰዋል፡፡ ሆኖም ተገቢውን ምላሽ ሊያገኙ እንዳ ልቻሉ ይገልጻሉ፡፡
በዚህ ምክንያት የተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ጥረት የሚያደርጉ አስተባባሪዎች ጉዳዩን ወደ ሚዲያ ለማውጣት ይቆርጣሉ፡፡ የሸገር ሬድዮ ጋዜጠኞችም ጉዳዩን ተማሪዎቹ ያሉበት አካባቢ ድረስ ሄደው ይዘግቡታል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ከሌሎች በተለይም አስተባባሪዎቹ በሌሎች ዩኒቨ ርሲቲዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚማሩት ጋርም ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የሚ ያደርጉትን የመብት ጥያቄና እንቅስቃሴ አብረዋ ቸው የሚማሩ ካድሬዎች (እነሱ ሰርጎ ገቦች ይሏ ቸዋል) ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ለሶስተኛ አካል (ለመንግስት) መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ከተቃዋሚ ዎች ጋርም ግንኙነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ ይህ መረጃ ለመንግስት አካላት መድረሱንም መረጃው ከደረሳቸው መካከል ውስጥ አዋቂዎች መልሰው ለአስተባባሪዎቹ ይነግሯቸዋል፡፡ አስተባባሪዎቹ የሚያነሷቸው የመብት ጥያቄዎችም ወደ አመጽ ሊቀይሩት እንደሆነ በመግለጽ መታሰር እንዳለባ ቸው መወሰኑን ይገልጻሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም እስ ራትና አፈና ሊደርስባቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡
አስተባባሪዎቹ ‹‹ፖለቲካዊ ጥያቄ መጠየቅ መብ ታችን መሆኑን አላጣነውም፤ ነገር ግን የአሁኑ ጥያ ቄያችን የመብት እንጂ ፖለቲካዊ ጥያቄ አይደለም›› ይላሉ፤ አክለውም ሊታሰሩ እንደሚችሉ የውስጥ ምንጫቸው በእርግጠኝነት እንደነገራቸው ይገል ጻሉ፡፡
ወጭ መጋራት በስምምነታቸው ላይ ያልነበረ ቢሆንም አሁን ግን እንደገና መጥቷል፡፡ መምህር ከሆናችሁ በአገልግሎት ዘመን፣ ሌላ ስራ ከሰራ ችሁ በገንዘብ ትከፍላላችሁ ተብለዋል፡፡ ይህ ግን ስምምነቱ ላይ አልነበረም እንደተማሪዎቹ ገለጻ፡፡ ‹‹እንዲያው ይህን ስምምነት እንሙላ ከተባለ እንኳን የሚሰጡን አገልግሎቶች ሊሟሉልን ይገባ ነበር፡፡ አሁንም ያቀረብነው አገልግሎቶች እንዲሟ ሉልን የሚል ነው፡፡ ያቀረብናቸው ቅድመ ሁኔታ ዎች ከተሟሉ ወጭ መጋራቱን ልንፈርም እንችላ ለን፡፡ እነሱ ግን በሚገባ ጥያቄያችን ሊመልሱልን አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ምግብና ሌሎች አቅርቦቶች እንደማይሰጠን፣ ትዕዛዙ ከትምህርት ሚኒስትር የመጣ በመሆኑ ካልፈረሙ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ልንሄድ እንደሚገባ ሁሉ አስፈራርተውናል፡፡›› የሚለው ደግሞ የስፖርት ሳይንስ ተማሪና እንቅስቃሴውን ሲመራ የቆየው ሚሊዮን ታደሰ ነው፡፡
በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት ተማሪዎች መብታቸውን ስለጠየቁ ሁለት ቀን ምግብ ከልክለው ጾም እንዳዋሉዋቸው ይገልጻሉ፡፡ በፖሊስ እያስደበደቡም ከግቢ አስወጥተዋቸዋል፡ ፡ ‹‹ባልተዘጋጀንበት ሁኔታ ትምህርቱን ጥለን አንሄ ድም!› ብለው መኖሪያቸው ቁጭ ቢሉም በፖሊስ ተከበው በመደብደባቸው በግድ የወጭ መጋራቱን ለመሙላት ተገደዋል፡፡ ከጅማ ውጭ በሌሎች ዩኒ ቨርሲቲዎች የሚገኙት ተማሪዎች የወጭ መጋራት አልሞሉም፡፡ በሶስቱ ዪኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳርና ወላይታ ሶዶ) የወጭ መጋራት አልተጠ የቀም፡፡ እነሱም ግን መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ ጅማ በግድ ሞልተዋል፡፡ ሌሎቹ ጋር በግዳጅ እንዲሞላ ጫና እየተደረገ በመሆኑ ያልተጠየቁትንም እንዲሞሉ ያስገድዷቸዋል፡፡››
ለተማሪዎቹ የተሰጠው ምላሽ በዚህ አያበቃም፡ ፡ ‹‹መብት ብላችሁ መጠየቅ የለባችሁም፡፡ አርፋችሁ ተማሩ›› ተብለናል፡፡ የወጭ መጋራቱን እንድንሞላ ለማስገደድ ከትምህርት ሚኒስትር ሳይቀር ሰዎች እንደተላከባቸውን ይገልጻሉ፡፡
አስተባባሪዎቹ ተማሪዎችን በማስተባበር የምንመደበው መሰረታዊ ወጭዎችን አሟልተን የማንኖርበት መምህር ነት፤ መንግስት እያዋረደው፣ ህዝብም እየናቀው ባለ ሙያ ውስጥ ልንገባ ተጨማሪ እዳ አንገባም ይላሉ፡፡ ተማሪዎቹ እንደሚሉት መንግስት አስተባባሪዎቹን በማሰር ጉዳዩን አድበስብሶ ለማለፍ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ‹‹በእኛ በኩል ምላሽ ካልተሰጠን ትምህርት ማቆምና ሰላማዊ ሰልፍ የማ ድረግ እርምጃዎችን እንወስዳለን፡፡ ምግብ ሊከለክሉን አይችሉም፤ ይህ በእኛ እና በአባቶቻችን ስም ተለምኖ የመጣ ነው›› በማለት መብታቸውን አሳልፈው እንደማይ ሰጡም ይናገራሉ፡፡ የዝግጅት ክፍላችን ድረስ መጥተው ስለጉዳዩ መረጃ የሰጡት የእንቅስቃሴው መሪዎች የሚከ ፈለውን መስዕዋትነት ከፍለው መብታቸውን እንደሚያስ ከብሩ ገልጸውልናል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ
http://www.goolgule.com/students-of-aau-are-demanding-their-right-to-be-respected/
No comments:
Post a Comment