Opposition Voice
Friday, April 18, 2014
እውን ወያኔ አባይ ወንዝ እንዲገደብ ይፈልጋል?
ከደበበ ኃይሉ
የአባይ ወንዝን ገድቦ ለኢትዮጵያውያኖች ጥቅም የማዋሉ ፍላጎት ዛሬ የተጀመረ አይደለም። በታሪክ
የምናውቃቸው የኢትዮጵያ መሪዎች ሁሉ የዚሁ የአባይ ወንዝ መገደብ ምኞት ተገዢዎች ሆነው አልፈዋል።
አጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሃንስና አጼ ሚኒልክ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከግብጽ ጋር ተነታርከዋል፣ ጦር ሰብቀው
ተዋግተዋል። የውሃ ማማ ሆና የተጠማች ኢትዮጵያ ብቻ ነች። የአባይን ልጅ ውሃ ጠማት የአሳዛኝዋ
ኢትዮጵያ መገለጫ ሆኗል።
ወያኔ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ሊከፋፍልና ሊጎዳ ብሎም ከምድረገጽ ለማጥፋት የምድረበዳው አጋንንትን
ወክሎ፣ የዘመኑን ንድፈ-ሐሳብ ተከትሎ ከግብጽ ተነስቶ በሰሜኑ የሃገራችን በኩል የመጣ መንፈሳዊ ጠላት
ነው። የታሪክ አጋጣሚ፣ የጊዜ ማጋደል ድጋፍ ሆነው እንጂ ወያኔ አንዳች አጋር የለውም። ኢትዮጵያውያን
እጆቻቸውን ወደ እግዚአብሄር እንዳያነሱ በውሃ ጥምና በረሃብ እያዳሸቀ ለሰይጣን ግርማ ሞገስ የሆነው ወያኔ
የኢትዮጵያ ሕዝብ መንፈሳዊ ጠላት፣ የዲያቢሎስ ተባባሪ የሰይጣን ቁራሽ አካል ነው። ወያኔን ጨቋኝ
መንግሥት፣ አምባገነነ መንግሥት አድርጎ በዲሞክራሲ ትግል ለመጣል የሚደረገው ትግል የወያኔን መንፈሳዊ
ጠላትነት አበጥሮ ያለመረዳት ችግር ነው። ወያኔ ሃሳቡንና እቅዱን ለመተግበር በክርስትያኖቹ የትግራይ ልጆች
መንፈስ አድሮ እንዲሁም የግብጽ ሠለባ የሆኑትን ኦብነግ፣ ኦነግና ሻዕቢያን ተመርኩዞ ኢትዮጵያን
ሊያመሰቃቅል ግብጽ የዘር ልዩነትና የጎሳ ግጭት አስታጥቃ የላከችው ጠላት ነው።
የአባይ ወንዝ መገደብ የእግዚአብሄር ሃሳብ፣ ኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ ዘመናትን የጸለዩበት የአምላክ ዕቅድ
መፈጸምያ ነው። በዘመኑ መጨረሻ የአባይ ወንዝ ለመድረቁ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እነሁ ቃሉ ይፈጸም
ዘንድ አንዳች ኃይል የማያግደው አምላክ የምድረበዳው አጋንንት አምልኮና ፍልስፍና መነሻ የሆነችውን
ግብጽን ወደ ምድረበዳነት ለመመለስ አባይን ማድረቁ አይቀሬ ነው። እንኳንስ እንደትል የሚርመሰመሱት
ምሁራንና ልህቃን፣ አስማተኞቹ፣ ሞገደኞቹ ሞራ ገላጮች ይቅሩና የኃላኖቹ የጦርና የኒውክለር ኃይል፣
ቴክኖሎጂ፣ ፍልስፍናና ሳይንስ ይሄን የአምላክ ቃል ሊቀለብስ አይችልም።
ታድያ ወያኔ ግብጽ ልካው እንዴት ግብጽን ይጎዳል? ይህ የሕዝብ ጠላት፣ የመልከጼድቅ አገር የሆነችው
ኢትዮጵያ ጠላት፣ የአባይን ወንዝ የመገደብ ኃይል አግኝቷል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ የሙስና
መንግስት አባይን ገድቦ ለሱዳን ሊሸጥ ይሆን? ይህ ርኩስ መንግስት አባይን ገድቦ ቀሪውን ሕዝብ በአፍዝ
አደንግዝ ተብትቦ ወደ ትግራይ ሊከልል ይሆን? ወይንስ ይህ የወያኔ መንግስት በጥፋቱ ተጸጽቶ
ለኢትዮጵያውያኑ አስቦ ይሆን? ወይንስ እግዚአብሄር ወያኔን የቃሉ መፈጸምያ አድርጎት ይሆን አባይን ያህል
ግድብ ለመገንባት ዕድሉን የሰጠው? ይሆን ይህ ሁሉ ምስጢር ወደፊት የሚገለጽ ነው። እመለስበታለሁ።
የሆነስ ሆነና ገና ድሮ መውደቅ የሚገባው ወያኔ የስልጣን ዕድሜው እንዴት ሊራዘም ቻለ?
1. ወያኔ በዓይነጥላም ይሁን መተት በትግራይ ክርስትያኖችና ጀግኖች ልብ ውስጥ አድሮ ገና ከጅምሩ ከሻዕቢያ
ተባብሮ ኢትዮጵያውያንን በተከዜ በረሃው መንፈስ አማሎ የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዲድ)
የሚል የደቂቅ ጋኔኖች ማጠራቀምያ ከረጢት ሠፋ። ኦሕዲድ በውስጡ ያደረው ቀበጥባጣው ጋኔን ባቃሰተው
ቁጥር ኦሮምያ ክልሏ ተቆረሰ እያለ ከማቧረቅ አንስቶ የጡት ሃውልት እስከመገንባት የደረሰ ወያኔ ከሰይጣን
ትምህርቶችች እንኳን ትንሽቱን ያላቋደሰው ሞኝ ድርጅት ነው። ይህ ተላላ ድርጅት ወያኔ እየሳቀ
የሚጋልብበት የሜዳ አህያ ሆነ። ሰሞኑን ፋሲል የኔአለም "አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት" የሚለውን ቀልድ
ተዉትና ለእውነተኛ የነጻነት ትግል ተነሱ የሚለውን ቁምነገረኛ ጽሁፍ ቢያነቡት አንዳንዶች ማስተዋል
ይሆናቸዋል።
2. ወያኔ በአምሳሉ የፈጠራቸው የተቃዋሚው ድርጅት አባሎች ለትናንሽ ፍርፋሬ ሲሉ ኅልውናቸውን የሸጡ
የዋሆች ናቸው። የወያኔው ሠይጣናዊ አገዛዝ ዲሞክራሲያው እንዲመስል ቀለማማውን ግምዣ የተሸከሙት
እነዚህ ተንቀሳቃሽ ፍጡራን ለወያኔ ዕድሜ መራዘም ምክንያት ናቸው።
3. በእውነተኛ ተቃዋሚዎች ውስጥ ሠርገው የገቡት አስመሳዮችና የወያኔ ሰላዮች የተቃዋሚውን ስልትና ዕቅድ ንድፍ ጠልፎ በማስጠለፍ የወያኔን ዕድሜ ያራዝማሉ።
4. በውጭ የሚደረገውን የድጋፍ ኃይል በማጨናገፍና በማዳከም "ግንቦት ሰባት" የወያኔ ዕድሜ እንዲራዘም
ትልቅ አስተዋጾ አድርጓል። በቅርብ ቀን ከአስመራ ተነስቼ ሥልጣኑን እይዛለሁ ያለው የሰባት ዓመቱ "ግንቦት
ሰባት" በርካታ ጉጅሌዎችን በውስጡ በማቀፍ - ብርሃኑ ነጋን የሚያጅቡ የጉራጌ ጉጅሌዎች፣ አንዳርጋቸውን
የሚያጅቡ የጎጃም ጉጅሌዎች፣ ኤፍሬም ማዴቦን የሚያጅቡ የደቡብ ጉጅሌዎች፣ ታማኝን የሚያጅቡ የጎንደር
ጉጅሌዎች እንደፈነጥዙና እንዲቦርቁ በማድረግ ትግሉ እንዲዘናጋ፣ የእውነተኞቹ ተስፋ እንዲሟጠጥና የወያኔ
ዕድሜ እንዲራዘም አድርጓል። ግንቦት ሰባት - ይህን ዓይነቱን አሠራር የቀዳው ቀድሞ ሲያገለግልለት
ከነበረው ወያኔ ባህርይ እንዲሁም ዛሬ የበሬ ግንባር ታህል ሜዳ ካኮናተረው ሻዕቢያ ነው። ግንቦት ሰባት
በውጭ ሃገር ሥነ-ምግባርን ያልተለማመዱ ቦዘኔዎችንና የሱስ ተገዢዎችን ከፊት በማስቀደም ስብዕናን የሚነካ
ነቀፋ እያስወረወረ ባላባትነቱን ለማግዘፍ ይሞክራል።
5. ወያኔ ዕድሜው እንዲራዘም ምዕራብያኖቹ እጅግ ትልቅ ንዋይ ይልኩለታል። ይህም ኃይማኖት
እንዲዳከም፣ ሞራል እንዲላሽቅና ስነ-ምግባር እንዲበላሽና ኢትዮጵያዊነት እንዲጠፋ ነው።
6. የወያኔ ዕድሜ እንዲራዘም አስተዋጾ ካደረገው ትልቁ ጉዳይ አንዱ ዲያስፖራው ወደ ዘመዶቹ የሚልከው
ትልቁ የውጭ ምንዛሬ ነው። ይህ የውጭ ምንዛሬ የወያኔ ዋነኛው ገቢ ሆኗል። ለጠላት ጠመንጃ መግዢያ
ገንዘብ እየላኩ ጠላትን ከሩቅ በመዋጋት ረገድ አዲስ የውጊያ ስልት የፈጠረው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ነው።
7. የውጭ ተቃዋሚዎችና ወያኔ ስደቱ እንዲስፋፋ ይፈልጋሉ። ይኸውም ስደተኛውን ሰለባቸው በማድረግ
የገንዘባቸው ምንጭ እንዲሆን ነው። ስደቱ ለወያኔውም ሆነ ለግንቦት ሰባት ታላቅ የገንዘብ ምንጭ ነው።
8. ወያኔ ብዙዎችን በተበላሸ የሥነ-ልቦና መንፈስ በመተብተብ የአማራ ጠላት አድርጎ ማስነሳቱ ሆኖለታል።
"አማራ" ማለት ኢትዮጵያ አንድ ነች ብለው የተነሱት የልዩ ልዩ ነገድና ጎሣ አባላት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ዶርዜው፣ ከንባታው "ኢትዮጵያ" ካለ "አማራ" ነህ ይሉታል። ኦሮሞው፣ ሲዳማው፣ ወላይታው፣ ሲናሻው
"ኢትዮጵያ" ካለ "አማራ" ይሉታል። "አማራ" የሚለው ቃል የዲያቢሎስ ወያኔ የማጥቂያና የመከፋፈያ መንፈስ
እንዲሁም የጥቃት አድማሱን ማስፍያ ስልት ነው።
9. በውጭ ሀገር ትግሉን የተደባለቁ፣ ኢትዮጵያን የማይወዱት አንዳንድ ኤርትራዎችና ኦሮሞዎች በዲያቢሎስ
መተት ተተብትበው፣ "አማራ ወይም ኢትዮጵያ" የሚለውን ቃል በመጠየፍ የየራሳቸውን አካሄድ
አበጃጅተዋል። በኢትዮጵያውያን መካከል ክፍፍሉ እንዲበራከት በክፋት፣ በንዴት፣ በጥላቻና በቂመኝነት
ውስጥ ውስጡን በማድባት መርዝ ይረጫሉ፣ ያጋጫሉ፣ ያፌዛሉ። ይህ ድርጊት በኢትዮጵያውያን መሀከል
ውጣ ውረድ፣ ጥርጣሬና አመጻ እንዲስፋፋ ያደርጋል።
10. በጓደኝነት፣ በጋብቻና በጥቅማጥቅሞች ሳብያ የኢትዮጵያን ጠላቶች የሚደግፉና እጉያቸው አቅፈው
"አይዟችሁ" የሚሉት ተላላ ኢትዮጵያውያን ትግሉ እንዲራዘምና የውጭ ኃይሎች እንዲቦርቁ የመንገዱ ቀያሽ
ከሆኑ ሰንብተዋል። እነሱም እንደ ኦሕዲድ የውጭው የኢትዮጵያን ጠላቶች መጋለብያ ሆነዋል።
ወያኔ እንዴት ይወድቃል?
ወያኔ እግዚአብሄር ባዘጋጃቸው እውነተኞችና ሃቀኞች ኢትዮጵያውያን ትግል ይወድቃል። የጠላትን አሠራር
መገንዘብ፣ እምነትና ጽናት እንጂ ወያኔ በስልት፣ በነገር፣ በቧልትና በአጀብ አይወድቅም። የእግዚአብሄር ዕቅድ
ሲፈጸም ወያኔ ወድቆ በረከትና ሠላም ወደ ሃገሪቱ ይፈሳል። ከሕዝባዊው ሠልፍ አንስቶ በቃሊቲና ዝዋይ
እስከታጎሩት ሃቀኞች ጽናት ድረስ ኢትዮጵያ አንድ ሃገር፣ አንድ ሕዝብ ነች። ኢትዮጵያውያን የጠላትን ሃሳብና
ዕቅድ በቅጡ ሲረዱ ወያኔ ይወድቃል። ከሃዲዎችንና አመፃን የሚያስፋፉትን ማስተማርና መመለስ
ያስፈልጋል። ልህቃኑ "ለልታይ ልታይ" ፍላጎታቸው ማርኪያና ለዓላማቸው ፍጆታ የሚያውሉትን የሥነ-ልቦና
ብረዛና ሃሰተኛ ትምህርት ጠንቅቆ መለየትና መዋጋት ያስፈልጋል። እግዚአብሄር ይመስገን።
ጸሃፊውን በ debebehailu321@gmail.com ማግኘት ይቻላል
http://www.ethiolion.com/Pdf/04182014Abay.pdf[1].pdf
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment