April 26, 2014
ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም… እየተዘፈነ ይገኛል።
ከሚደመጡ መፈክሮች መካከል….
ከሚደመጡ መፈክሮች መካከል….
ተርበናል፣ ተጠምተናል፣ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት አልቻልንም!
——————————————————–
—————————
—————————-
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሽሮ ሜዳ፣ መነን ፒያሳ፣ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ፣ መርካቶ፣ አብነት፣ ልደታ፣ ሜክሲኮ፣ሸበሌ፣ ብሄራዊ፣ ለገሀር ስታዲየም፣ መገናኛ፣ ኮተቤ፣ ሀያ ሁለት ፈረንሳይ፣ ቦሌና ሌሎችም የአዲስ አበባ ክፍሎች በእግርና በመኪና የተሳካ ቅስቀሳ አድርገው ተመልሰዋል፡፡ ፖሊስ በመኪናም ሆነ በእግር የሚቀሰቅሱትን ለማስቆም ጥረት ቢያደርግም አባላቱ ቅስቀሳውን አከናውነው ተመልሰዋል፡፡ (ነገረ-ኢትዮጵያ)
—————————
ከሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተላለፈ መልዕክት
ነገ የራሳችሁንና የቀሪ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ ለማሰማት ወደ ሰልፉ የምታቀኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባዶ ጀሪካን፣ ባዶ ስልክና ሻማ ይዛችሁ እንድትመጡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከትግላችን ሰላማዊነት ጋር የማይቃረኑ፣ ከኢትዮጵያዊ ባህልና ወጋችን ያላፈነገጡ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የሚያገልግሉና መብትን ለማስመለስ ምልክቶች የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ይዛችሁ በሰፍልፉ መገኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ለሰላማዊ ሰልፉ መገኘት የማትችሉ ኢትዮጵያውያን በተለይም በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ባገኛችሁት መንገድ ሁሉ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኘው ህዝብ መልዕክት በማስተላለፍ መብታችን ለማስመለስ በምናደርገው ትግል የበኩላችሁን ሚና መጫወት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ራሳችን ከፍርሃት ነጻ አውጥተን ሰላማዊ ትግሉን ካልተቀላቀልን ሁሌም ከሰው በታች ሆነን እንገዛለን፡፡ በፍቅር፣ በቆራጥነት፣ በኢትዮጵያዊ ወኔ የተነጠቁትን መብቶቻችን ማስመለስ አለብን፡፡ ኑ የተነጠቁትን መብቶቻችን በማስመለስ የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!
———————————
ሰማያዊ ፓርቲ የዞን ዘጠኝ አክቪስቶችንና ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ እየተደረገ ያለውን እስር አጥብቆ ያወግዛል! በነገው ስልፍም ይፈቱ ዘንድ ድምጹን ያሰማል!
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልሳለን›› በሚል ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ከምናነሳቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ገዥው ፓርቲን ላይ የሠላ ትችት ስለሰነዘሩና ለህዝባቸው መረጃ ስለሰጡ ብቻ የሚደርስባቸውን ህገ ወጥ እርምጃ ያወግዛል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ የህዝብን መብት ለማስመለስ ለጠራነው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 50 ያህል አመራሮችና አባላት በህገ ወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የፓርቲያችን ሊቀመንበር (ማታ ተፈትተዋል)፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ አክቲቪስቶችና ሌሎች ጋዜጠኞችም ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሌሎችን ለማሰር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዥው ፓርቲ ከፍርሃት የመነጨ አምባገነናዊ እርምጃ በጽኑ ይቃወማል፡፡ በነገው ዕለትም በእነዚህ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ላይ የተደረገውን እስር የሚያወግዝ መሆኑን መግለጽ ይወዳል፡፡
ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!
——————————-
ዝግጅቱ ተጧጡፏል ፡፡ ሁሉም ስራ ላይ ነው!
ነገ በሰለፉ ለይ የሚገኘውን ህዝብ ለማስተባበር ሁሉም በየድርሻው በቢሮም በተለያዩ አካባቢዎችም የመጨረሻ ስራዎችን እያከናወኑ ነው፡፡ ቅስቀሳም በተለያየ መልኩ ቀጥሏል፡፡
ኑ በአደባባይ ተቃውሟችንን በመግለፅ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ!
ሰማያዊ ፓርቲ!
No comments:
Post a Comment