Opposition Voice

Opposition Voice

Saturday, April 5, 2014

በደሴ ፖሊስና የደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች የሰላማዊ ሰልፉን ቅስቀሳ ለማደናቀፍ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀረ




April 5th, 2014
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረቦች ክስተቱን በፎቶግራፍ አንስተዋል
—————–
የአንድነት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተውን የቅስቀሳ ቡድን ተግባር ለማደናቀፍ ፖሊሶችና ደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች በስውር ቪዲዮ በመቅረፅ እና ስለሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የሚስተጋቡ መፈክሮችን ለማስቆም ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይም የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ቅስቀሳው በተደረገባቸው ስፍራዎች በመገኘት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማስፈራራትና ከቅስቀሳ ቡድኑ አባል ላይ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ለመንጠቅ ሲሞከር በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የማደናቀፍ ሙከራ ቢደረግም ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ የደሴ ህዝብ ከአንድነት ፓርቲ ጎን በመሆን ቅስቀሳውን አጧጡፎታል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች(አቶ ተክሌ በቀለ፣ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ እና አቶ ሃብታሙ አያሌው) ከቅስቀሳ ቡድኑ አባላት ጋር በመሆን በመኪና ላይ የድምፅ ቅስቀሳ፣ በራሪ ወረቀት እደላና ፖስተር በመለጠፍ ላይ ናቸው፡፡ እንደተለመደው የደሴ ህዝብ የተለመደ ድጋፉን ለአንድነት ፓርቲ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡10246832_835736313109498_4232990120556389759_n
10246832_835736313109498_4232990120556389759_n (1)
10174963_835669536449509_993779596150300973_n
10155823_835669356449527_3760871470725215523_n
10152391_835736339776162_7351371086334858666_n
10015653_835736346442828_702939082745029919_n
1979707_835669559782840_4884275559750355297_n
1932212_835669419782854_217415443982846583_n
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/13835

No comments:

Post a Comment